ባለሙያዎች የጤና አገልግሎት እየሰጠን ስንታመም የምንታከመው ግን በራሳችን ወጪ ነው

የጤና አገልግሎት እየሰጠን ስንታመም የምንታከመው ግን በራሳችን ወጪ ነው”የህክምና ባለሙያዎች

ጤና መድህን
ጤና መድህን ለጤና ባለሙያዎች

የጤና መድህን ለጤና ባለሙያዎች

“የጤና ባለሙያዎች አገልግሎቱን እንዲያገኙ የሚያስችል ጸድቆ የመጣ መመሪያ የለም”ጤና ሚኒስቴር

የጤና አገልግሎት እየሰጠን ስንታመም የምንታከመው ግን በራሳችን ወጪ ነው ሲሉ የህክምና ባለሙያዎች ገለጹ። የጤና ሚኒስቴር በበኩሉ ለተለያዩ ህመሞች ተጋላጭ ለሆኑ ባለሙያዎች የተለየ ገንዘብ ክፍያ ከመፈጸም ውጪ በባለሙያዎቹ የተነሳውን ቅሬታ ለመፍታት የሚያስችል ጸድቆ የመጣ መመሪያ የለም ብሏል።

.

ቅሬታቸውን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያቀረቡት ባለሙያዎቹ እንደገለጹት፤ በርካታ ተግዳሮቶችን በማለፍ የህክምና አገልግሎት ለሕዝቡ እየሰጠን ብንገኘም በምንታመምበት ጊዜ ግን በራሳችን ወጪ ነው የምንታከመው። ይህም ወጪው ከአቅማችን በላይ ሲሆን ለምነን ለመታከም ተገደናል ይላሉ።

.

የኢትዮጵያ ህክምና ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶክተር ተግባር ይግዛው እንዳሉት፤ የጤና ባለሙያዎች በህክምና ሥራቸው ላይ ለሚገጥም ህመም ህክምና የሚያገኙት በሚቀጥራቸው የህክምና ተቋም ይሁንታ ላይ በመመስረት እንጂ በሕግ የተደገፈ መብት የላቸውም።

.

የጤና ባለሙያው ህመም ሲገጥመው የሚታከምበት ሕጋዊ የሆነ ማዕቀፍ እንደሌለው ያመላከቱት ዶክተር ተግባር፤ ይህም ህክምና ማግኘት መብት ይኑረው ወይም አይኑረው የሚያረጋግጥበት ሁኔታ የለም ብለዋል። ዶክተር ተግባር አንዳንድ የጤና ተቋማት ሠራተኛ ስለሆኑ ብቻ በመልካም ፍቃድ የተወሰኑ ነገሮችን በነፃ ሊያክሙ እንደሚችሉ የጠቆሙ ሲሆን ይህ ግን ለባለሙያው ሕጋዊ መብት እንደማይሰጠው ጠቅሰዋል።

.

ዶክተር ተግባር አንድ በሀገሪቱ የትኛውም ስፍራ ላይ ያለ የጤና ባለሙያ ባለበት አካባቢ ላይ እንደምንም አገልግሎት ቢያገኝ እንኳን ወደ ሌላ አካባቢ ሲሄድ አገልግሎት እንደማያገኝ በመጥቀስ፤ ይህም የጤና ባለሙያዎች የሚሰጡትን አገልግሎት ለራስ መንፈግ የሞራል ጥያቄ ያስነሳል ብለዋል።

Social health insurance will start this year 2015 EC

ለጤና ባለሙያ የሚሰጠውን አገልግሎት በነፃ እንዲያገኝ ማድረግ በጤና ዘርፍ ላይ ያለውን ጥራትና ዘመናዊነት ለማስጠበቅ ስለሚኖረው ጉልህ አስተዋፅኦም ዶክተር ተግባር ጠቅሰዋል። የጤናው ዘርፍ የዓመታት ዕቅድ ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎትን በሁሉም ስፍራ የማዳረስና በገንዘብ ምክንያት አገልግሎት የሚያጡ ዜጎችን መታደግ መሆኑን የገለጹት ዶክተር ተግባር፤ በሀገራት ተሞክሮም የጤና መድን መተግበር የሚመከር መሆኑን ገልጸዋል።

.

የጋምቢ ሜዲካል ቢዝነስ ኮሌጅ ባህርዳር ካምፓስ ዲን ዶክተር አዱኛ ጣሰው በሰጡት አስተያየት እንዳሉት፤ የጤና ባለሙያዎች የሚሠሩበት ተቋም ሊደግፋቸው ካልተንቀሳቀሰ በቀር ሲታመሙ በነፃ የሚታከሙበት የተደራጀ ሥርዓት የለም። የጤና መድህን ጉዳይ በየመሥሪያቤቱ የሚሠራበት ሂደት መኖሩን የጠቀሱት ዶክተር አዱኛ፤ይህ አሠራር በጤና ተቋማት ባለመዘርጋቱ የህክምና ባለሙያዎች ችግሮችን በመጋፈጥ ላይ ናቸው ነው ያሉት።

. 🩺🩺

በጤና ሚኒስቴር የሰው ሀብት አስተዳደር የሠራተኛ አገልግሎትና ማበረታቻ ቡድን መሪ ወይዘሮ ፍቅረሰላም ጋሜ በሰጡት ምላሽ እንዳሉት፤ ለተለያዩ ህመሞች ተጋላጭ ለሆኑ የጤና ባለሙያዎች የተለየ የገንዘብ ክፍያ ከመፈጸም ውጪ በባለሙያዎቹ የተነሳውን ቅሬታ ለመፍታት የሚያስችል ጸድቆ የወጣ መመሪያ የለም ብለዋል።

.🩺🩺🩺

እንደ ኃላፊዋ ንግግር፤ ተጋላጭ የሥራ ክፍል ውስጥ ያሉ ማለትም በንክኪ በትንፋሽና በደም ለሚተላለፉ በሽታዎችን ለሚያክሙ የጤና ባለሙያዎች የተለየ ገንዘብ ይከፈላቸዋል። ተጋላጭ እንዳይሆኑ የሚያስችሉ ግብዓቶችም ይቀርብላቸዋል። ከዚህ ውጪ የጤና ባለሙያዎች ህመም በሚገጥማቸው ወቅት የተለየ ክፍያም ሆነ የጤና መድህን የሚያገኙበት በፅሁፍ የተደገፈ መመሪያ የለም ሲሉ ጠቅሰዋል::

መረጃ ምንጭ :- አዲስ ዘመን ህዳር 15/2016

ምንጭ  መድህን


የቅርብ ልጥፎች

Addis ababa university vacancy

Teklehaymanot general hospital vacancy

Girum General Hospital vacancy announcement

Yonan Agency vacancy announcement

Comments

One response to “ባለሙያዎች የጤና አገልግሎት እየሰጠን ስንታመም የምንታከመው ግን በራሳችን ወጪ ነው”

  1. Tigist mathewos Avatar
    Tigist mathewos

    Arifnew

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Please do not infringe copyright!